Back to Archive
Official Publication

በሙያ ስራ ላይ ለተሰማሩ የህግ ታራሚዎች የክህሎት ማረጋገጫ ስልጠናና እውቅና ለመስጠት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ

Authorized Byabdi
Release DateCaamsaa 12, 2026
በሙያ ስራ ላይ ለተሰማሩ የህግ ታራሚዎች የክህሎት ማረጋገጫ ስልጠናና እውቅና ለመስጠት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ
በሙያ ስራ ላይ ለተሰማሩ የህግ ታራሚዎች የክህሎት ማረጋገጫ ስልጠናና እውቅና ለመስጠት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ gallery 1
በሙያ ስራ ላይ ለተሰማሩ የህግ ታራሚዎች የክህሎት ማረጋገጫ ስልጠናና እውቅና ለመስጠት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ gallery 2
በሙያ ስራ ላይ ለተሰማሩ የህግ ታራሚዎች የክህሎት ማረጋገጫ ስልጠናና እውቅና ለመስጠት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ gallery 3
በሙያ ስራ ላይ ለተሰማሩ የህግ ታራሚዎች የክህሎት ማረጋገጫ ስልጠናና እውቅና ለመስጠት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ gallery 4

Executive Abstract

""

የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የህግ ታራሚዎችን ለነገው ህይወታቸው በማዘጋጀትና ወደ ማህበረሰቡ በብቃት እንዲቀላቀሉ ለማስቻል እየተከናወነ ያለውን የሪፎርም (የእርምት) ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል።

የዚህ ስራ አካል በሆነውና በተለያዩ የልማት መስኮች በተለይም በጀጎል ኮሪደር ግንባታ ላይ በተግባር ስራ ላይ ለተሰማሩ ታራሚዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና በመስጠት የክህሎት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ለማበርከት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ዛሬ ሰፊ የጋራ ውይይት ተደርጓል።

​መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናን አህመድ እንደገለጹት፣ የታራሚዎችን የእርምት ቆይታ ውጤታማ ለማድረግና ከማረሚያ ቤት ሲወጡ በሰለጠኑበት ሙያ ተሰማርተው ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።

ኮሚሽነሩ አክለውም፣ የታራሚዎቹን የተግባር ልምድ በንድፈ-ሀሳብ በማጠናከር ሰርቲፋይ የማድረጉ ሂደት በፖሊቴክኒክ ኮሌጆችና በሚመለከታቸው የዘርፍ ተቋማት አማካኝነት የሚከናወን መሆኑን ጠቁመዋል።

​የመድረኩ አስተባባሪና የተሃድሶ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አብራሂም ዑመር በበኩላቸው፣ ይህ የተቀናጀ አሰራር ታራሚዎች ያላቸውን ክህሎት ወደ ተቀመጠው የሙያ ደረጃ (Standard) በማምጣት፣ ወደ ማህበረሰቡ በሚቀላቀሉበት ወቅት የስራ ዕድል በቀላሉ እንዲያገኙ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።

Authenticated Document Archive

© 2026 Harari Prison Police Commission • All Rights Reserved