Back to Archive
Official Publication

በሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በተሻሻለው የአመክሮ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ::

Authorized Byabdi
Release DateMay 12, 2026
በሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በተሻሻለው የአመክሮ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ::
በሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በተሻሻለው የአመክሮ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ:: gallery 1
በሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በተሻሻለው የአመክሮ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ:: gallery 2
በሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በተሻሻለው የአመክሮ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ:: gallery 3
በሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በተሻሻለው የአመክሮ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ:: gallery 4

Executive Abstract

""

​የሐረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከተገልጋይ የህግ ታራሚዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እንዲሁም አዲስ በጸደቀው የአመክሮ አሰጣጥ መመሪያ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

​በመድረኩ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ እና የዕቅድና ፕላን ዳይሬክተሩ አቶ ታምራት የተገኙ ሲሆን፣ የህግ ታራሚዎች ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች (የጽዳት፣ የጤና፣ የምግብና የስነ-ስርዓት ኮሚቴዎች) እና በየክፍሉ የተመረጡ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

​በውይይቱ ወቅት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ እንቅስቃሴና አፈጻጸም ዝርዝር ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ የታራሚ ኮሚቴዎች በዕቅዱ አፈጻጸም ዙሪያ ያላቸውን ምልከታና የሥራ ሂደት በሰፊው ተወያይተውበታል።

​ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ተሻሽሎ የጸደቀውን የህግ ታራሚዎች የአመክሮ አሰጣጥ መመሪያ በተመለከተ ለታራሚዎቹ ማብራሪያ የስጡት ኮሚሽነር አድናን አህመድ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የአመክሮ አሰጣጥ ክፍተቶችን ለመቅረፍ መመሪያው መሻሻሉን እና አዲሱ መመሪያ የአመክሮ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ታሳቢ ያደረጋቸው. በኮሚሽኑ የሚሰጡ ልዩ ልዩ የሙያ ስልጠናዎች ላይ በንቃት መሳተፍ፣

​በመደበኛ ትምህርት ዘርፍ ተሳታፊ መሆን፣

​በቆይታቸው የሚያሳዩት መልካም ስነ-ምግባር እንደሆነ ገልፀዋል።

​ኮሚሽነሩ አክለውም አመክሮ በዘፈቀደ የሚሰጥ ሳይሆን፣ በታራሚው ጥንካሬና ለውጥ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚሰጥ መሆኑን አስገንዝበው በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ከታራሚዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ኮሚሽነር አድናን አህመድ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፣ ውይይቱ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

Authenticated Document Archive

© 2026 Harari Prison Police Commission • All Rights Reserved